top of page

ስለ ማህበራችን
የኢትዮጵያ ካናዳውያን አዛውንቶች ማህበር በኦታዋ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊ አረጋውያንን ችግር ለመፍታት ትኩረት ያደረገ የመጀመሪያው ማህበር በመሆን በሚያደርገው ጥረት ከፍ ያለ እርካታ ይሰማናል፡፡
ማህበራችን የዋና ከተማዋን መሰረት በማድረግ በጥቅምት 2018 ዓ.ም መልካም አሳቢና ትጉህ ግለሰቦች ተነሳሽነት የተቋቋመ ነው። መስራቾቹ ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ አገልግሎቱን ተደራሽ እያደረጉ ይገኛሉ።
የማህበሩ ስኬት የጀርባ አጥንት የቦርድ አባላትና በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃደኞች ጥረት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በወር አንድ ጊዜ በማእክላችን ብሮንሰን ማዕከል እንሰባሰባለን። በቀጣይ ያሉ መርሃ ግብራትን ለማወቅ የጊዜ ሰሌዳችንን ይመልከቱ።
የኢትዮጵያ ካናዳውያን አዛውንቶች ማህበር በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን ይቀበላል። በአሁኑ ወቅት ለወጣቶች ወርሃዊ ዝግጅቶችን እናካሂዳለን። በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ የተሻለ የትምህርት፤ የስራና የህይወት ልምድ ያላቸው የማህበራችን አባላት ተሞክሮ የማካፈልና የልምድ ልውውጥ ስራ እናካሂዳለን።
bottom of page