top of page

UPCOMING
EVENTS

ለመላው የማህበራችን አባላት በሙሉ ከዚህ ቀደም ባከናወነው የመሠረተ ቴክኖሎጂ ፕሮግራም ላይ በልጆቻችን እገዛ የተዋጣለት የኮምፒውተር ስልጠና ለአባላቶቻችን መስጠታችን የሚታወስ ነው፣ በዚህም ፕሮግራም ወላጆች ከልጆቻቸው ዘመኑን የሚመጥን የመሠረታዊ የኮምፒውተር እውቀት ከማግኘታቸው ባሻገር የነበራቸው መቀራረብ እና እርስ በእርስ በደንብ እንዲተዋወቁ ምክንያት በመሆን በስኬት ተጠናቋል።
በአሁኑ ሰመርም በተለየ መልኩ ፕሮግራም ያዘጋጀን ሲሆን ይኸውም ልምድ እና ሙያው ባላቸው አባትና እናቶች የማንነታችን መሠረት የሆነውን ጠንካራ እምነታችንን፣ ባህላችንን፣ ሀገራችንን፣ ታሪካችንን እና በመሳሰሉት ርእሶች ላይ ትምህርት ይሰጣሉ። የዚህ ፕሮግራም ዋነኛው አላማ ልጆቻችን በመንፈስም ሆነ በአካል ጠንካራ ሆነው ከመጥፎ ምግባሮች ተቆጥበው ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለሀገራቸው መልካም ዜጎች እንዲሆኑ ለማስቻል ለምናደርገው ጥረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን፣ ለዚህም መልካም ምግባር መላው የማህበሩ አባላት የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ በአክብሮት እንጠይቃለን። ስለፕሮግራሙ ዝርዝር አፈፃፀም በተከታታይ በሚወጡ ማስታወቂያዎች ማብራሪያ እንሰጣለን።

በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ሁሉ 'ባርኮዱን' ስካን በማድረግ ወይንም ደግሞ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ልትመዘገቡ ትችላላችሁ።
https://forms.office.com/r/3F1anqeVZZ

በተጨማሪም ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የመጠየቁን ቅጽ ወይም Questionnaire Form በመሙላት ለፕሮግራሙ መሳካት አስተዋጾ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።
https://forms.office.com/r/QXAANM0EFd

Manenete
Summer 2024 Event
bottom of page